• Skip to main content
  • Skip to primary sidebar

Africa Horn Now

"We don't take sides; we help you see more sides."

Africa Horn Now

ካብ ውሽጢ ቤት ማእሰርታት ኤርትራ

Published: May 6, 2021

PBS: Escaping Eritrea … [Read More...] about ካብ ውሽጢ ቤት ማእሰርታት ኤርትራ

ካልተስማማን እንደሀገር እንጠፋለን

March 4, 2016 By Africa Horn Now

ግርማ ካሳ |  March 3, 2016 | ከአዲስ ገጽ እትም ስድስት የተወሰደ

በግምት ከሃያ አራት ዓመታት በፊት ይሆናል ቀኑ። በኢትዮጵያ እርቅና ሰላም እንዲኖር ብዙ ጊዜ የሚደክሙና የሚጸልዩ፣ ቄስ ቶሎሳ ጉዲና የሚባሉ አንድ መንፈሳዊ አባት፣ ምዕመናንን ሲያስተምሩ የተናገሩት፣ ሁልጊዜ የማስታወሰውና የማልረሳው አባባል ነበር።

«አዲስ አበባ አንድ ወዳጄ አርፎ ለቀብር ሄድኩኝ። የወዳጄ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ካለቀ በኋላ ሌሎች ወደ ቤታቸው ሲመለሱ እኔ በዚያው ቆየሁ። በመቃብሩ ቦታ ያሉትን ኃውልቶች እያየሁ በድንጋዮቹ ላይ የተጻፉትን የሟቾቹን ስምና መንፈሳዊ ጥቅሶች ማንበብ ጀመርኩኝ። ዞር ስል አንዱ መቃብር ላይ የትግሬ ስም አየሁ። ሄድ ብዬ ደግሞ እንደኔው በ ”ሳ” የሚያልቅ የኦሮሞ ስም ያለበት ኃውልት አጋጠመኝ። የአማራም የሚመስልም አለ። እንግዲህ አስቡት … ትግሬውም አማራውን ኦሮሞውም … ሁሉም በሰላም ተኝተዋል» ሲሉ እኝህ መንፈሳዊ አባት የታዘቡትን ተረኩ። ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነ መጀመሪያ ላይ አልገባኝም ነበር።

ዓይኖቻቸውን ወደ ምዕመኑ አድርገው «ሙታን አርፈው በሰላም ጸጥ ብለው ተኝተዋል። እኔ ትግሬ ነኝ፣ አንተ አማራ ነህ፣ ደግሞ ጉራጌ ሆነህ እኔ ጋር ምን ታደርጋለህ? እያሉ አይገፋፉም። በሰላም ጸጥ ብለው ነው ጎን ለጎን የተኙት» ሲሉ ትምህርታቸውን ቀጠሉ።

ምዕመናን በተመስጦ ያዳምጡ ነበር። እኝህ አባት ለትንሽ ጊዜ ዝም አሉና ከኪሳቸው ውስጥ ማህረባቸውን አወጡ። በዓይናቸው ላይ የነበረውን እንባ ጠረጉ። ትልቅ ትንፋሽ ተንፍሰው «ታዲያ … እኛ በሕይወት ያለን ሕያዋን፣ በእግዚአብሔር እንድንዋደድና እንድንፋቀር፣ አንዱ ለሌላው እያዘነና እየተከባበርን እንድንኖር በመልኩና በአምሳሉ ፈጥሮን፣ ሁላችንም የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን፣ ሁላችንም ኢትዮጵያዊ ሆነን፣ እንዴት አብረን ተፋቅረን በሰላም መኖር ያቅተናል? ስለምን ሰውን በስብዕናውና በኢትዮጵያዊነቱ ከማክበርና ከመቀበል ይልቅ በዘር እየተከፋፈልን እንደጠላት እንተያያለን?» በማለት ለምዕመናኑ ጥያቄዎች አቀረቡ። «ይኼ መርገም ነው። ይኼ በሽታ ነው። ይኼ ከሙታን የባሰን እንደሆንን የሚያሳይ ነው። እግዚአብሔር ከዚህ እርግማን ያውጣን! እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያንም መልካም ጣቶቹን ዘርግቶ ይፈወሳት?» ሲሉ፣ ምዕመናን ከተቀመጡበት ብድግ ብለው «አሜን» አሉ።

ከሃያ ዓመታት በፊት ደግሞ ሌላ የሰማሁት አንድ ታሪክ ነበር። ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ከዘር ጋር በተገናኘ መዘዝ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ማለቃቸው መቼም የሚረሳ አይደለም። (አሁንም ያ አይነት ችግር በሀገራችን አለ)

ያኔ በበደኖ፣ በአርባጉጉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ኢትዮጵያውያን፣ ከኛ ዘር አይደላችሁም ተብለው፣ በጭካኔ ከመቶ ሜትር በላይ በሚሆን ገደል ውስጥ አይናቸው በጨርቅ ተሸፍኖ፣ ነፍሰ ጡር የሆኑ ሴቶች ሁሉ ሳይቀር ተወርውረዋል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቤታቸው ውስጥ እያሉ እንዲቃጠሉ ተደርጓል። በጣም የሚያሳዝንና የማይረሳ ግፍ በኢትዮጵያዎኖች እጅ ኢትዮጵያውያኖች ላይ ተፈጽሟል።

የቂም በቀልና የዘረኝነት ደመና አገሪቷን በሸፈነበት በዚያን ወቅት፣ በኢሊባቡር ክፍለ ሃገርም ተመሳሳይ ሁኔታ እንዲፈጠር በዘራቸው ምክንያት ዜጎች ይጠቁ ዘንድ የሚገፋፋ ርካሽ ቅስቀሳ ማድረግ ተጀመረ። (“አማራ” የሚባለው ከ”ኦሮሞው” ጋር እንዲገዳደል)
የሚያስደንቀው ነገር ግን በዚያ የሚኖሩ አበውና ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችን ሰብስበው «ለዘማናት አብረን ኖረናል። ተዋልደናል። ተጋብተናል። የነርሱ ልጆች የኛ ልጆች ናቸው። እነርሱን ማጥፋት እኛን ማጥፋት ነው» ብለው ፍቅርንና አንድነትን አስተማሩ። ለዚህ ይመስለኛል በአርባ ጉጉና በበደኖ የታየው አይነት እልቂት በኢሊባቡር ተፈጸመ ሲባል ብዙ ያልተሰማው።

ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ወደ ሆነ ሌላ አንድ አስደናቂ ታሪክ ልውሰዳቹህ። አገሩ በመካከለኛው ምስራቅ ነበር። ሁለት ህዝቦች ነበሩ። የመጀመሪያዎቹ አይሁዳውያን ይባላሉ። ሁለተኞቹ ደግሞ ሳምራውያን ይባላሉ። አይሁዳውያንና ሳምራውያን አይስማሙም ነበር። ፊት ለፊት ተያይተው እንኳን ሊነጋገሩ፣ አንዳቸው ወደ አንዳቸው ምድር አይደርሱም ነበር። በተለይም አይሁዶች ሳምራውያንን እንደሐጢያተኛ ይቆጥሯቸው ስለነበር፣ ከነርሱ ጋር ከተገናኙ እንደሚረክሱ አድርገው ነበር የሚያስቡት።እዚህ ላይ፣ በዚያን ወቅት የነበረው ባህልና ልማድ፣ የጥላቻ፣ የመናናቅና የዘረኝነት እንደነበረ እናያለን። በሰዎችና በሰዎች መካከል የሚለያይና የሚከፋፈል ሰው ሰራሽ ትልቅ ግንብ እንደነበረ እናያለን።

በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ አንድ ሰው፣ የነበረውንና የጊዜውን ሁኔታ ወደ ጎን በማድረግ፣ አይሁዳዊ ሆኖ ሳለ ሳምራውያን ወደ ሚኖሩበት ሰማሪያ ክፍለ ሃገር ያመራው። በዚያም አንዲት ሳምራዊት ሴትን፣ ሲካር በምትባል በሰማሪያ ባለች ከተማ በሚገኝ በውሃ ጉዳጋድ አጠገብ አገኛትና አናገራት። ውሃ ቀድታ እንድትሰጠው ጠየቃት።

ሳምራዊቷ ሴትም፣ ይህ አይሁዳዊ ሰው፣ እረክሳለሁ ብሎ ሳያስብ፣ ሳይፈራ፣ ከተለመደው ጎጂ ባህል ውጭ በመሆን እርሷን ማናገሩ በጣም አስገርሟት «አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለህ እኔ ሳምራዊቷን እንዴት ውሃ አጠጪኝ ትለኛለህ?» ስትል ጠየቀቸው።

ይህ ሰው ሙስሊም ወንድሞቻችን ኢሳ የሚሉት፣ ክርስቲያኖች የሆንን ደግሞ አንዳንዴ መድኃኒዓለም አንዳንዴ አማኑኤል ብለን የምንጠራውና የምናመልከው፣ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

«ሳምራዊ» ወይም «አይሁዳዊ» እያሉ በዘር መከፋፈል ሐጢያት እንደሆነና እግዚአብሔር እንደማይወደው ነው እዚህ ላይ የምናየው። በዚያን ወቅት የነበረውን ጎጂ የዘረኝነት ግድግዳ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያፈርሰው ነው የምናየው። ሰው ከስው ጋር በዘሩ ምክንያት መራራቅና መከፋፈል እንደሌለበት ነው የምንማረው። ሁሉም ሰው የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናቸው ወንድማማቾችና እህትማማቾች እንደሆኑ ነው የምናየው።

ብዙ ጊዜ ላለፍት በርካታ ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች ከዘር ጋር በተገናኘ በተማሪዎች መካከል ችግር መፈጠሩ በሰፊው ስንሰማ ነበር። በሀገራችን ባሉ ዮኒቨርሲቲዎች፣ ዜጎች በእውቀትና በትምህርት እንዲያድጉ የሚረዱ ተቋማት ናቸው። የአለም ህብረተሰብ ከዘረኝነት አልፎ በጋራ መሥራት በጀመረበት ወቅት፣ በሀገራችን ባሉ ዮኒቨርሲቲዎች ይህ አይነት ከዘር ጋር የተገናኙ ችግሮች መፈጠራቸው እጅግ የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ነው። የተማርን እንደመሆናችን የበለጠ መብሰልና ማገናዘብ ሲገባን፣ በሰይጣን መንፈስ የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ግለሰቦች ለግል ጥቅማቸው የሚያናፍሱትንና የሚቆሰቁሱትን የጥላቻና የዘረኝነት ፖለቲካን በማስተናገድ፣ ለጥቂቶች መጠቀሚያ እስክንሆን ድርስ ማስተዋል ማጣታችን ያሳዝናል። ምኑ ላይ ነው ታዲያ መማራችን?

የተለያዩ ቀለማት ባላቸው ክሮች የተሰራ ሹራብ ያምራል። ብርድና ንፋስ በመጣ ጊዜ ሲለበስ ይሞቃል። ነገር ግን እያንዳንዳችን አንድ ቀለም ለይተን ክሮችን መምዘዙንና መተርተሩን ከቀጠልንበት ክሮቹ ተመዘው፣ ተመዘው እርስ በርስ ተወሳሰበው ጥቅም የለሽ ይሆናሉ። ብርድ በመጣ ጊዜ ለብሰን የምንሞቅበት ሹራብ አይኖረንም። እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ካላደግን ሁላችንም አብረን እንጠፋለን።

እንግዲህ የዘር ፖለቲካ ይቁም! የሰብአዊ መብት ረገጣ ይቁም! ሕግ የበላይ ይሁን! የታሰሩ ሰላማዊ የሕሊና እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ! ሁላችንም ወደ እርቅ እንምጣ! ሁላችንም በዘር ሳንከፋፈል በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር እንሰባሰብ! እግዚአብሔር የሰጠንን አንዲት ኢትዮጵያ ከውርደትና ከማቅ ነጻ እናውጣት!

ለአንዳንዶቻችን ይህ ቅዠትና ሕልም ሊመስለን፣ በሽንፈትና በአይቻልም መንፈስ በመያዛችን በውስጣችን ለጨለምተኝነት ቦታ ሰጥተን ሊሆን ይችልል። አንዳንዶቻችን ደግሞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ሙሉ ለሙሉ ተስፋ የቆረጥን እንኖራለን። ነገር ግን ሁላችንም ልናያት የምንፈልገውን አዲሲቷን ኢትዮጵያ ማየት እንችላለን። እራሳችንን በራሳችን መመገብ እንችላለን። የሚያስፈልገው የልብና የአይሞሮ ለውጥ፣ መንፈሳዊ ፈውስና በአፍ ብቻ ሳይሆን በእውነትና በመንፈስ እጆቻችን ወደ እግዚአብሔር መዘርጋት ነው! «ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች» የተባለው የተስፋ ቃል ይፈጸም ዘንድ እኛ ኢትዮጵያውያን እጆቻችንን ከልባችን ጋር ወደ እግዚአብሔር እንዘርጋ!

በሳምራውያንና በአይሁዳዊያን መካከል የነበረውን ግድግዳ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳፈረሰው አሁንም በኢትዮጵያውያን መካከል ያለውን የዘረኝነትና የመከፋፈል ግድግዳ ያፈራርስልን! የይቅርታንና የመቀራረብን መንፈስ ያወርድልን! ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ ሳይሆን፣ ወንድሜ፣ እህቴ እንባባል። እግዚአብሔር ሁላችንንም ይርዳን!

Filed Under: TIGRINJA

Primary Sidebar

A New Administration Won’t Heal American Democracy

Published: November 6, 2020

The Rot in U.S. Political Institutions Runs Deeper Than Donald Trump Larry Diamond | November 5, 2020 | Foreign … [Read More...] about A New Administration Won’t Heal American Democracy

Archives

  • May 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • July 2020
  • June 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • June 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • April 2018
  • March 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • December 2017
  • November 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • December 2016
  • November 2016
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • July 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • February 2016
  • January 2016
  • December 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • July 2015
  • June 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • March 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • July 2014
  • May 2014
  • March 2014

Log In

Copyright © 2025 Africa Horn Now · WordPress · Log in