• Skip to main content
  • Skip to primary sidebar

Africa Horn Now

"We don't take sides; we help you see more sides."

Africa Horn Now

ካብ ውሽጢ ቤት ማእሰርታት ኤርትራ

Published: May 6, 2021

PBS: Escaping Eritrea … [Read More...] about ካብ ውሽጢ ቤት ማእሰርታት ኤርትራ

ዛሬ ኢትዮጵያ የምትሄድበትን መንገድ እያየን የነገ መውጫውን ካሁኑ መተለም የግድ ይላል

January 4, 2017 By Africa Horn Now

December 23, 2016 | zehabesha

አሁንም ስለ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ በጣም በጥልቅ አስባለሁ። የችግሩ ብቻ ሳይሆን የመፍትሄው አካልም እኔ እራሴ እንደሆንኩ አስባለሁ።የብዙዎቻችን ችግር ችግሩን የማንሳት እንጂ የመፍትሄው አካል ለመሆን ምን ላድርግ የሚል ኃላፊነት አለመውሰድ ነው።በእዚች እድሜዬ በቻልኩት ሁሉ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ ከመከታተል የቦዘንኩበት ወቅት የለም።መጨረሻ ላይ ግን አንጀቴን የሚባለኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።ሕዝብ ስል በፖለቲካው ዙርያ ተዋናይ የሆኑትን ብቻ አደሉም።ፖለቲካ ውስጥ ገብተው የሚሰሩ ከየትም አቅጣጫ እንበለው እነርሱም ፍቅር የሚሉት የእራሳቸው ነጥብ ይኖራል።ፖለቲካ ላይ ለጥቅም እና ለዝና ከገቡት ውጭ ሌሎች የህዝብ ፍቅር አስገድዷቸው የገቡ ናቸው ብዬ አምናለሁ።ይህንን መካድ አይቻልም።

አሁን በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ የሚታዩኝ አራት ችግሮች በደንብ እይተንፀባረቁ ነው።

1/ የኢትዮጵያ ዘለቄታ የፖለቲካ መፍትሄ ላይ አቅዶ አለመስራት፣

2/ ኢትዮጵያዊነትን ከማጠንከር ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን የሚያላሉ ተግባራት ላይ መሰማራት፣

3/ አሁን ያሉት ልዩነቶች አልበቃ ብሎ ለነገ ሌላ፣አዲስ እና ትኩስ ልዩነት ለመፍጠር መሞከር፣

4/ የነገዋ ኢትዮጵያ አሁን ካለባት የአምባገነን እና የጎሳ ፖለቲካ ወጥታ በትክክለኛ ፍትህ፣ዲሞክራሲ እና ሁሉን ያሳተፈ እንድትሆን ከመጣር ይልቅ አሁን ጀምሮ የእራስን ጎሳ እያገነኑ የነገ መሪ እኔ ነኝ ማለት፣

እነኝህ አራት ችግሮች የኢትዮጵያ የወቅቱ ችግሮች ናቸው።ችግሮቹ አሁን በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ብቻ የሚቀነቀኑ ሳይሆኑ በነገዋ ኢትዮጵያ ላይም ተመሳሳይ ችግር እንዲፈጠር ሕልም እና ምኞት እንዳላቸው ከማኅበራዊ ድረ-ገፅ አንስቶ እስከ መድረክ ንግግሮች ድረስ የሚያንፀባርቁ አካላት በትክክል እየታዩ ነው።ከአሁኑ ይልቅ በነገው ላይ የሚሰራው ሥራ ነው አሳሳቢው።¨ከትናንት ብንዘገይ ከነገ እንቀድማለን¨ የምትለው አባባል ልትዘነጋ አይገባም።የኢትዮጵያ ነገር ውስጣችንን የሚያቆስለን በድፍረት ልንጋፈጣቸው የሚገቡ ብዙ ሺህ ጉዳዮች ከፊታችን እንዳሉ መዘንጋት የለብንም። የፌስ ቡክ ንትርኩ አንዳች ጉዳይ አይፈይድም።ይልቁንም ለነገዋ ኢትዮጵያ ሁሉንም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሳይል የሚበክል የጎሳ ማግነን ሃሳቦች አሁን ያለነውን ብቻ ሳይሆን መጪውን ትውልድ እንዳይበክል መስራቱ ነው ቁም ነገሩ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የነገ መጪ እጣ ግን አንገብጋቢ ነው።መፍትሄ የሌለን ሕዝብ ልንሆን ፈፅሞ አንችልም።ነገን አሻግረን ከተመለከተን የመፍትሄው አካል የሆነው የዛሬ የተግባር ግዴታችን ይገባናል።እውነትን፣ፍቅርን እና ፅናትን አለመያዝ ብቻ ነው የመፍትሄ ድሃ የሚያደርገን።ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ስናወራ የነገውን የሚያስብ እንጂ አሁን ላለው ስሜት ማስታገሻ ብቻ መሆን የለበትም።

አንድ ማወቅ የሚገባን ጉዳይ የሥርዓት ለውጥ አይቀርም።በባሌም በቦሌም ብሎ አይቀርም።ለለውጥ የሚሰራው ይስራ።ለለውጥ የሚሰራው በኃላ ይደርሳል ያላቸው ተግባራት ግን መስራት የሚገባቸው ብዙ ሺዎች ቁጭ ብለው ኢትዮጵያን አይን አይኗን ማየታቸው ነው ጥፋቱ።ለውጥ እንደሚመጣ እያወቅን ከአሁኑ ኢትዮጵያችን ነገ ብቻ ሳይሆን ከእዝያ በኃላም ደምቃ እንድትገኝ በእዚህም ሂደት ሁሉም ኢትዮጵያን ያለ ሁሉ እርስ በርሱ ሳይናከስ እና ማኅበራዊ ሰላሙ ከአሁኑ በባሰ መልኩ ሳይደፈረስ እንደ ሀገር መቀጠሉ ነው ወሳኙ ቁም ነገር። ይህ ደግሞ ከአሁኑ እየተገነባ ካልመጣ እና ሁሉም ወገን በጋራ የሚያምንባቸው ሃሳቦችን እያጎላን ካልመጣን ነገ በይድረስ ይድረስ የሚሰራ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በእውነትም ያሳዝናል (ከእራሴ ጨምሮ)። ምሁራኑ አዲስ ሃሳቦች አፍልቆ፣ ከስልጣን ጥማት እና ከማታለል ፈፅሞ በራቀ መልኩ የሕዝቡን ደካማ አስተሳሰቦች እያበረቱ፣እይታውን እያጠነከሩ እና ከክፍለ ዘመን ወደ ክፍለዘመን በቀላሉ የምትሸጋገር ኢትዮጵያን ለማምጣት አሁን ላይ የመፍትሄ ሃሳብ አምጠው መውለድ እና ወደ ሥራ መግባት የምሁራኑ የውዴታ ግዴታ ነው።የኢትዮጵያ ምሁራን ከሀገር ቤት እስከ ባህር ማዶ ያላችሁ ለነገዋ ኢትዮጵያ የሚሰራ የመፍትሄ ሃሳብ በቶሎ ውለዱ እንጂ የእኔ ጎሳ ነገ ኢትዮጵያን ይገዛል ብላችሁ ያለፈ ችግር የሚደገምባት ኢትዮጵያን እንድናይ አታድርጉ።ይህንን ሃሳብ በሚገባ ተንጠርጥሮ መቅረብ እንዳለበት አምናለሁ።ወደፊትም በጊዜው ጊዜ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

ኢትዮጵያን መውደድ ማለት፣ህዝብን መውደድ ማለት የእራስን ጎሳ ብቻ ማምለክ አይደለም።የምንኖረው 21ኛው ክ/ዘመን ነው።ይህ የዘመን ቁጥሩ ብቻውን ከጎሳ የፀዳ ዓለም እንደማያሳየን የታወቀ ነው።ዓለም የፈለገውን ሊዘፍን ይችላል።እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ከጥንት ጀምሮ አለምን ያስተማርነው ብዙ የፍቅር ታሪኮች አሉን።በወቅቱ የተለየ እምነት ይዘው ከመካ የመጡትን የመሐመድ ቤተሰቦች ጀምሮ እስከ ከዓለም ዳር በክርስትናቸው ምክንያት የተሰደዱትን ዘጠኙን ቅዱሳን የተቀበልን እስከ አሁን ድረስም አሻራቸውን በኢትዮጵያ እንዲያሳርፉ እና አካላችን እንዲሆኑ ያደረግን ድንቅ ህዝቦች ነን።ዓለም በጎሳ ስላበደ አሜሪካን ሀገር የጥቁር እና የነጭ ችግር ስላለ፣በኢትዮጵያ ታሪክ ያልታየ የጎሳ መንግስት አራት ኪሎ ላይ ስልጣን ስለያዘ መሰረታዊ የአስተሳሰባችን መጠን ሊዛነፍ አይገባም።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከትግራይ እስከ ሞያሌ፣ከአኮቦ እስከ ፈርፈር ግራ ተጋብቷል።የሚሰማው ሁሉ ጆሮውን እየጠለዘው ልክ አሁን ያየውን ችግር ያህል ነገም እንዳይደገም የመፍትሄ ሃሳብ የሚሰጠው ወገን እየጠበቀ ነው።አጫጭር ስሜት የሚኮረኩሩ፣ የእኔ ጎሳ የበለጠ ጀግናው የሚሉ ፉከራዎች ለነገ አብሮ የመኖር ሕልውናችን ዋስትናዎች አይደሉም።ዛሬ ኢትዮጵያ የምትሄድበትን መንገድ እያየን የነገ መውጫውን ካሁኑ መተለም የግድ ይላል። ለእዚህም የመፍትሄ ሃሳብ መውለድ ያስፈልጋል ።

Filed Under: TIGRINJA

Primary Sidebar

A New Administration Won’t Heal American Democracy

Published: November 6, 2020

The Rot in U.S. Political Institutions Runs Deeper Than Donald Trump Larry Diamond | November 5, 2020 | Foreign … [Read More...] about A New Administration Won’t Heal American Democracy

Archives

  • May 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • July 2020
  • June 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • June 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • April 2018
  • March 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • December 2017
  • November 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • December 2016
  • November 2016
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • July 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • February 2016
  • January 2016
  • December 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • July 2015
  • June 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • March 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • July 2014
  • May 2014
  • March 2014

Log In

Copyright © 2025 Africa Horn Now · WordPress · Log in