PBS: Escaping Eritrea … [Read More...] about ካብ ውሽጢ ቤት ማእሰርታት ኤርትራ
“ብዕር ከጎራዴ ይብልጣል”
ትኪ ጉደታ | August 6, 2016 | ዘሐበሻ
ሰሞኑን በሚገርም ሁኔታ ወልቃይት-ጠገዴ-ጠለምት የመከራ ግፍ እና ስደት ለበርካታ ኢትዮጵያን ከራስ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ነው የዘለቀው:: በ1990 ዓ/ም በአንድ አአ ዩንቨርሲቲ የመኝታ ክፍል የምንጋራ እኔ ከአርሲ ነፍሱን ይማረውና ተስፋዬ ጨመዳ ከወለጋ ተስፋዬ አፍጮ ከመርካቶ (ዛሬ ደሜ “blood type T”) ብሎ በ150 ብር ስጦታ በዳግማው ምኒልክ ት/ት (በ1993 ዓ/ም) ስብሰባ ላይ ተገዝቶ ሕወሓት ሳይሆን በፊት ጎጃሜው (ለደነንቱ ስል ስሙን ዘልየዋልሁ) ተጋሪያችን ያወጋን በነበረ ወቅት ነው ስለ አማራ-ትግሬ መሬት ነጤቃ የሰማሁት:: ጉዳዩ እንዲ ነው “አማራ መሬት ተርፎት ነው ወይ ለትግሬ ከወሎ እና ከጎንደር የሚሰጠው?” የሚል ጥያቄ በብአዴን ስብሰባ ላይ (በ1990 ዓ/ም) ጎጃሜው በማንሳቱ ከፍተኛ ሰቆቃ እንደተፈፀመበት አውግቶን ነበር፡፡ እንደውም በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ልከው ለማስገደል ሲሞክሩ ጎጄው መርጃው ሲደርሰው ወድያው የብአዴን አባል በመሆን ከሞት ተርፎ እንደውም ፀባዩን በማሳመሩ ምክነያት (በህወሐት አባባል ለማለት ነው) እስከ ሦስተኛ ዲግሪውን (PhD) እንዲሰራ በመደረጉ ልሳኑ ታፈነ፡፡ እኔ ደሞ ከ6 ዓመት በፊት ትግራይን በሙሉ ለሁለት ወር ለመጎብኘት ጉዞ ባደረኩበት ግዜ የታዘብኩት ነገር ከተከዜ ወደ ጎንደር ከአዲ ዐርቃይ ጀምሮ ያለው መሬት በእውነት በጣም ለም መሬት መሆኑን ማየት ብቻ በቂ እንደሆነ ታዘብኩ:: ነገሩ እስደጋጭ የሆነብኝ ቀሪውን ትግራይ ሳይ ነው፡፡ በእውነት የሰው ልጅ እና መሬት ያላቸውን ቁርኝት ለማወቅ ይከበዳል፡፡ ያን የመሰለ ትሁት ሕዝብ እዛ መሬት ላይ መኖር መቻሉ ተዐምር ነው ይሆነብኝ:: በቃ አፈሩ ያለቀበት ደንጋይ የበዛበት ጎርበጥባጣ መሬት ነው፡፡ እኔ የትግራይን ህዝብ ከዛ በኋላ ሳስብ አንጀቴን ይበላኛል፡፡ ግን ደሞ ህወሐት የሰራው እየሰራም ያለውን ወንጀል እንድደግፍ አያደርገኝም:: አውስትራሊያ እና ሰሜን አሜርካ ያገኝኃቸው ወልቃይት-ጠገዴ-ጠለምት አዛውንት ልብ የሚንካ ታሪክ አውግውትውኛል፡፡ እንዲሁም ከሕወሓት ጋ ያለውን ሁኔታ ልመታዘብ ሞክሬ የግመትኩት ነገር የወሰደውን መሬት አይመልስም የሚል ነው ምክንያቱም፡-
1. ከማይ-ፀብሪ ጀምሮ በርካታ የቀድሞ የሕወሓት ተጋደላይ ሰፍረውበታል እነዚ ሰዎች በድርጅቱ ላይ ከፍትኛ ትፅኖ ሊያደርሱ የሚችሉ ጥያቄዎች ያቀርባሉ ተብሎ ሊፈራ ይችላል፡፡ ማስፈራሪያዬ ናቸው ብሎ ስለሚያስብ ማስቀየም አይፈልግም::
2. ህወሐት በሀብትና በሌላ ጎሳ መበልጥ አይወድም፡፡ ይህ የተቀማ መሬት ደሞ ሁለቱንም የያዝ ስልሆ ከሕወሓት የጅል ባሕሬ ሁኔታ መመለስ አይችልም፡፡ ያው የነብር ጅራት አይያዙ…..ነው ነገሩ :: በእውቀት ጉዳይ ሕወሓት ዜሮ ስለሆኑ የውቅት መበለጥ በብር ለመግዛት የሚጥሩ ናችው፡፡
እንደ እኔ መፍትሄ ይሆናል የምለው እስከ መጨረሻው ለማውረድ መጣር:: ወታደሩን በፍቅር መስበክ ከስሜታዊነት የፀዳ መልክቶችን በተቻለ መጠን ሕዝቡን ለማስተማር መጣር ከፍተኛውን ድርሻ መያዝ አለበት፡፡ በተጨማሪ አማራጭ ከሕዝብ ጋር መገናኛ መንገዶች መፈለግ አለበት ሕወሓት ከአቅሙ በላይ ሲሆን ስልኩንም ሌላውንም ሊዘጋ እና ይህንን የተነሳሳ ፈላጎት ረገበ አድርጎ የማሰቢያ ግዜ ለመገዛት ይችል ይሆናል፡፡ አሁንም በትንሹ እያደረገ መሆኑ የሙከራ ምልክት ነው፡፡ እራሱንም ኪሳራ ውስጥ ቢከተውም ስልጣኑን ለማራዘም ሁሉንም ይሞክራል፡፡ሌላው የትግራይን ሕዝብ ብሶት እና ቅሬታ በድንብ መዘገብ እንዲሁም የሕወሓት/ኢህአዴግ ባለ ስልጣናት ሐብት በተቻለ አቅም ማጋለጥ እና ማሳወቅ ሕወሓትን ብቻውን እንዲቀር ማረግ እና አልፎም ያብላጫውን የሕዝቡ ልብ መግዛት ይቻላል:: በጣም ትልቁ ብዙ ትኩረት ያልተስጠው የኢትዮጵያ ሱማሌ በብዛቱ 3ኛ የሆነውን በሚያሳዝን ሁኔታ የተገፉ ወገኖቻችንን በተቻለ አቅም የሚመጣው ለውጥ እንደ ህወሐት መሬቱን ብቻ ሳይሆን እነሱም አካላችን እንደሆኑ በተቻለ ሁሉም ማሳወቅ የፖለቲካ እና የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊነት ብቻ ሳይሆ የሁሉም ዜጋ ስራ መሆን አለበት፡፡
ሕወሓት የሚፍራው ያልኖረበትን ብዕር ነው፡፡ ያም ስለሆነ ነው ለማሰር ያልቻለውን እንደ ታማኝ እና ሲሳይ ያሉትን ልቡ እንደ አበጠ ጎረምሳ በማስፍራራት የማይዘጋ ልሳን ለማዘጋት የማይታሰሩ እጆች ለማሰር ከርቀት የሞከረው:: ሁላችንም የቻልነውን ያህል ወደ መጨርሻው ግባችን ሊያደሪሰን ወደሚችለው እናተኩር እንደ ሰው ሙሉ ነትፃነት ሲኖረን ሁሉም በመነጋገር ይፈታል፡፡ ዶ/ር መረራ “ከአውራ ፓርቲ ወደ አውሬ ፓርቲ ሳይቀየር……” ብሎ ነብር ሰሞኑን:: እኔ ግን 600 በላይ ነፍስ በስምንት ወር ውስጥ የበላ ሕዋሓት ካውሬ በላይ ቃል ቢገኝ ያንስብኛል ያው ሴጣን ነው ልል የምችለው ደም የሚዎድ ሴጣን ስለሆነ፡፡ እናም ሲሳይ አጌና እዳለው እንዳይውድቅብን ለመጣል መውድቂያውን እናመቻች ከወደቀብን መነሳቱ እንዳይከብደን!!
PS: “ብዕር ከጎራዴ ይብልጣል” የሚለውን የተዋስኳት በጣም ደሳሳ ከሆነች ትንሽዬ ጉጆ ውስጥ የጭቃ ግድግዳ ላይ ተሰቅላ ያገኝኋት በምስራቅ ጉጃም ሶስቱን እነብሴዎች ለመጎብኘት በሔድኩ ግዜ ነበር፡፡
በዚህ ፅሑፍ ሕወሓት ነው ሊከፋው የሚችለው:: ያልከፋቹ ወገኖቼ ኢትዮጵያዊያን የኦሮሞ አማርኛ ስለሆነ የተገደፈውን ይቅርታ አስተካክላቹ አብቡልኝ፡፡
ትኪ ጉደታ ነኝ!!
ሕዋሓት እድሜህ ይጠርልን አሜን!!