Africa Horn Now

"We don't take sides; we help you see more sides."

Africa Horn Now
  • Home
  • AHN News
  • Seen/Heard
  • LIFE iN BaW
  • Insight
  • All articles
  • ትግርኛ/ አማርኛ
  • Svenska
  • CONTACT

የአቦይ ስብሃት ነጋ የሙስና ወጎች

January 29, 2017 By AHN

ክንፉ አሰፋ | undated | ኢትዮጵያ ዛሬ

በአሜሪካ አገር፤ አንድ ባለሥልጣን በሙስና ሲባልግ እስር ቤት ይገባል። በፊሊፒንስ አገር አንድ ባልሥልጣን የሙስና ወንጀል ቢፈጽም አሜሪካ ይገባል። የኛ አገር ባለግዜ ግን ሙስና ሲሰራ አሜሪካ እየተመላለሰ ይነግዳል። ለግዜው ልዩነቱ የዚህን ያህል ነው። ገለልተኛ የፍትህ አካል ባለበት አገር፤ ሙስና አፍ አውጥቶ አይናገርም፣ እግር አውጥቶም አይራመድም።

አዲሱ ቀልድ፤ “ሙስና አለ፣ ማስረጃ የለም!”

በያዝነው “ጥልቅ ተሃድሶ” ዘመን ሙስና ለሁለት ተከፍሎ እንዲታይ ተደርጓል። ማስረጃ ያለው ዘረፋ እና ማስረጃ የሌለው ዘረፋ። ልክ እንደ ግብር አከፋፈል። ግብር ከፋይ “ሀ” እና ግብር ከፋይ “ለ”። ምድቡ በዘረፋው መጠን እና በባለሥልጣኑ ጉልበት ይወሰናል። የዘረፋው መጠን ከአስር ሺህ በር በታች ከሆነ እና ዘራፊው የድል አጥቢያ ታጋይ ከሆነ ማስረጃ ያለው፣ ሙስና ምድብ “ሀ” ይሆናል። መጠኑ ከአስር ሚሊዮን በላይ ከሆነ ደግሞ ሙስና ምድብ “ለ” ተብሏል። ይህ አይነኬው ምድብ “ማስራጃ የሌለው ዘረፋ” መሆኑ ነው። አቅመ-ቢሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በብሄራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው የነገሩን ከዚህ እውነታ የተለየ አልነበረም። የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የፖሊት ቢሮ እና ምክትል ሚኒስትሮች ከአይነኬዎቹ ጎራ ይመደባሉ። የ4 ሺ ብር ደሞዝተኛ፤ ጄነራል የ10 ሚሊየን ብር ቪላ አሰርቶ ሲያከራይ በግላጭ እየታየ፣ “ማስረጃ የለም” ብሎ ማለፍ የሚያሳምን አይሆንም። የእያንዳንዱ ዘረፋ ማስረጃ፤ እዚያው አፍንጫቸው ላይ ነው ያለው። ግና የሚወሰነው በባለሥልጣኑ ጉልበት መጠን ነው። ምድብ “ለ”ዎችን ለመድፈር መሞከር ራሱ በሙስና ያስቀፈድዳል። ጸረ-ሙስና የሚባለውም ድርጀት የተፈጠረው ለእነሱ እና በእነሱው በመሆኑ የሚበየነውም የተገመደለ ፍርድ ነው።Sebhat Nega

ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ የዘረፉትን ባለሥልጣን ያጋለጡት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ፤ እስካሁን በተሰወሩ ባለ ግዜዎች ተገድለዋል። አቶ ተስፋዬ ከመገደላቸው በፊት ለጸረ-ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነሩ አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።ገዳዮቹ እኝህን ባለ ሃቅ፣ አሊ ሱሌማን ጋር እንኳን እንዲነጋገሩ እድል አልሰጧቸውም። የምህዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁም፣ በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም ላይ የነበረውን የገንዘብና የንብረት ሙስና የሚያጋልጥ ዜና በመስራቱ በከባድ የስም ማጥፋት ተወንጅሎ እስር ቤት ተወርውሯል።… አያሌ ጌታቸው ወርቁዎች፣ ብዙ ሳይታወቁ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ።

ስር የሰደደው የህወሓት ሙስና፣ ዛሬ ከዜጎች ንብረት እና ከመሬት ዝርፍያ አልፎ በቤተ-ጸሎት ውስጥም ዘው ብሎ ገብቷል። ከሚጓዝበት ከፍተኛ ፍጥነት አንጻር በዓአብያተ-ክርስትያናት እየተስፋፋ መሄዱ ብዙ አያስደንቅም። “ኃይለኛ” የሚል ስያሜ የተሰጠው የቁሉቢ ገብርኤል ዘረፋ እንደ ምሳሌ የሚጠቀስ ነው። ከመዕመናን በተደጋጋሚ የቀረበው የ30 ሚሊዮን የሙስና አቤቱታ ተለባብሶ እንዲያልፍ የጸረ-ሙስናው ቢሮ ትልቁን ስራ ሚና ተጫውቷል።

ለፖለቲካው ትኩሳት ማባረጃ ሰሞኑን የተሞከረው የኃይለማርያም ደሳለኝ የሙስና ተረት-ተረት ምላሹ ዝምታ መሆኑም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝም ብለው ጉንጭ አልፋ ቃላት እንዳባከኑ መገመት አያድግትም ። በዝምታ ውስጥ ያለው ጩሀት ግን ሳያስፈራ አልቀረም። እየተካሄደ ስላለው ነገር ሁሉ ብቸኛው መንገድ ዝምታ ነውና ያስፈራል። ጸጥ ባለ በዚህ ባህር ውስጥ ትናንሽ እና ትላልቅ አሳዎች እንደልባቸው ይዋኛሉ።

የቀድሞ የህወሓት አመራር አባል የነበሩት አቶ ገብሩ አሥራት “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚለው መፅሐፋቸው ስለ ሙስናው ሲጠቅሱ፤ “.. .መርማሪ አቋቁመን ሥር ሰዷል የተባለውን ሙስና ስንመረምር የት እንደገባ የማይታወቅ 5 ሚሊዮን ብር ተገኘ። ለዝርፍያው ተጠያቂዎቹም ግርማይ ካህሳይ የሚባል ሒሳብ ሰራተኛ እና ተክለ ወይኒ ነበሩ። … ይህ በሆነ ግዜ ተክለ ወይኒ ተነስቶ ‘ይህ ኮራፕሽን እያላችሁ የምታደርጉት ምርመራ ትክክል አይደለም፤ የተከሰተው ችግር የአሰራር ግድፈት እንጂ ሙስና አይደለም፤ እያንዳንዱ የህወሀት አመራር አባል ቢፈተሽ ተመሳሳይ ግድፈት ሊገኝበት ይችላል። …ዓባይ ፀሐዬ ደግሞ ከሁሉም የባሰ ሙሰኛ እንጂ ሙስናን ሊታገል የሚችል ሰው አይደለም'” ማለቱን ጠቅሰዋል።

በኢሕአዲግኛ ቋንቋ የሚሊዮኖች ዘረፋ፤ ሲተረጎም የአስተዳደር ብልሹነት ሳይሆን ይልቁንም አነስተኛ የአሰራር ጉድፈት ነው። ይህንን ጥቂት ጉድፈት ደግሞ የማይሰራው የህወሓት ሰው የለም ነው እያሉን ያሉት። ለዚህ “ከገለባ የቀለለ” ጥፋት ታዲያ ከሳሽም፣ ተከሳሽም ሆነ ዳኛው አንድ አካል ነው።

ታላቁ መጽሐፍ እንዲህ ይለናል፤

“… ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ። በመካከልም እርሱዋን አቁመው። ‘መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?’ አሉት። …. መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።”

እነሆ አቦይ ስብሃት ነጋ ስለ ሙስና ይነግሩናል። ደጋግመው ይነግሩናል። ሙሰኞች መጥፋት አለባቸውም ይሉናል። ሙሴ በአዖሪት እንዳዘዘው ሁሉ ‘ታላቁ መሪ’ ስኳር ያሉትን የኪራይ ሰብሳቢነት ቫይረስ ለማጥፋት – የሌባው እጅ ይቆረጥ በለዋል። ትእዛዙ ተፈጻሚ አይሆንም እንጂ፣ ቢሆንማ ኖሮ የመጀመርያዋ ሰለባ “ቀዳሚዋ እምቤት” ነበሩ። ፉከራው ካንገት በላይ በይሆን ኖሮ የሁሉም ህወሓት ሰዎቸ እጅ ዱሽ በሆነ ነበር።

ታዲያ ከሃጥያቱ ያልጸዳ ከየት ተገኝቶ የመጀመርያ ድንጋዩን ይወርውር?

“ዝምታ ወርቅ ነው” እንዲሉ አቦይ ስብሃት ከአንገት በላይ ከሚቀባጥሩ ይልቅ እንደው ዝም ቢሉ ያምርባቸዋል።

የአቶ ስብሀት ነጋ ልጅ ተከስተ ስብሀት ነጋ፤ ግዙፉን የጎተራ አደባባይ ለአምስት ዓመት ኮንትራት በ600 ሺህ ብር እንደወሰደው ፎርቹን ጋዜጣ ይፋ አድርጎታል። የ’አክሊል ክሬቲቭ ኤጄንሲ’ ባለቤት የሆነው ተከስተ ስብሀት ነጋ፤ በአካባቢው ያለን 4000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር፣ በቢሊየኖች የሚገመት መሬት እንደ ስጦታ ነው የወሰደው። ልጃቸው X-5 (አሁን ኤክስ አሙሽተ ተብሏል) ለወዳጆቹ በስጦታ እያበረከተ፣ አባቱ ሙሰኞችን እናጥፋ ሲሉ ይቀልዱብናል። “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ! …”

አቦይ ስብሃት ነጋ ደርሶ፣ አይኑን በጨው አጥቦ ኢትዮጵያ እንዴት በሙስና እንደምትፈራርስ ጋዜጣዊ መግለጫም ይሰጣል። ከጥፋቱ ድፍረቱ። የዚህን አዛውንት የሙስና መረብ ያጋለጠ አንድ ጥናታዊ ጽህፍ ስለ ስብሃት ነጋ ዘረፋ ሌላም የሚነግረን ነገር አለ። ህልቆ መሳፍርት ከሆኑት ዘረፋዎች ጥቂቶቹን ብቻ ለመጥቀስ፤

አድማስ ዩኒቨርስቲ ኮለጅ ባለቤት አቶ ይብራህ፣ የአቶ ስብሃት የአክስት ልጅ ነው። ይህ ሰው ያለ አንድ መነሻ ካፒታል በአዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች አድማስ በሚል 16 ካምፓሶች ያሉት ኮሌጅ ከፍቷል። ኮ/ል በላይ ነጋ ደግሞ የአቶ ስብሃት ወንድም ናቸው ። እኝህ ሰው ከወንድማቸው ባገኙት የህዝብ ገንዘብ በአዲስ አበባ፣ በመቀሌ እና በዓድዋ የዘመናዊ ፎቅ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል። ከዜሮ ተነስተው በብርሃን ፍጥነት የመጠቁት የኮ/ል በላይ ነጋ ሃብት በዚህ አያበቃም። በጋምቤላም የሰፊ እርሻ ቦታ “ኢንቨስተር” በመሆን የሜካናይዝድ ግብርና ኩባንያ ባለሃብት ሆነዋል። እኚህ ቢሊዮነር በቃሊቲም ግዙፍ ኩባንያ ገንብተው ነበር። ግን ምን ያደርጋል ዘረፋውን ገና ሳያጣትሙት ሞት ነጠቃቸው። ነብስ ይማር! አቶ በላይ ነጋ ሲሞቱ፣ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ሃብቱን በውርስ ተረክባዋለች። … እንዲህ እያልን ስንዘረዝር ብንወል የዘረፋው ተሳታፊዎች ቁጥር አንድ መጽሐፍ ይሞላል።

ድንቅ ነው። «ኢህአዴግ ሙሰኞችን ካልከሰሰ አገሪቷ ወደ ብተና ማምራቷ አይቀርም!» ይላሉ ስብሃት ነጋ ምንም ሳይሳቀቁ። በልባቸው ግን እየሳቁ! እኚህ ሰው ስለ ሙስና አስከፊነት የመናገሩን ሞራል ከየት እንዳመጡት እንጃ። ያንን ሁሉ ጉድ በአናታቸው ላይ ተሸክመው እንደው ዝም ቢሉስ ምን አለበት? አበው እንዲህ ይመክራሉ “የምታወጣቸው ቃላት ከዝምታ የተሻሉ መሆናቸውን ስታውቅ ብቻ ተናገር።” አቶ ስብሀት ነጋ በአንድ ወቅት፤ “በኢትዮጵያ በተጨባጭ ያለው ሙስናን ለማጥፋት ፍላጎት እንጂ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ብሎ ነገር የለም።”ብለውም ነበር። ይህ አባባል ግምሽ እውነታ አለው። በእርግጥ ፍላጎቱም ቁርጠኝነቱም ቢኖር ኖሮ አቦይ ስብሃት ከአይቴ ነጋ ገብረ-እግዚአብሔር ጋር መኖርያቸው በከርቸሌ ይሆን ነበር ። አንዳንዴ ጸረ-ሙስና የሚሉት ድርጅታቸውን አፈንጋጮችን (ትናንሽ አሳዎችን) ለመምቻ ይጠቀሙበታል።

“ዶክተር” አቦይ ስብሃት አድባባይ እየወጡ በተናገሩ ቁጥር ፣ በሳቸው ሳምባ የሚተነፍሱት ኃይለማርያም ደሳለኝም በ”አይቅርብኝ” አፋቸውን ሞልተው ስለሙስና ይናገራሉ።

እርግጥ ነው። የመንግሥታዊ ሌብነቱ ደረጃ ጥግ ላይ ደርሷል። እየዘረፉ ደግሞ ህዝብን ባይገድሉ ምን ነበረበት? ከዘረፋው የከፋ ሌላ ትልቅ ወንጀል አለ። ከህዝቡ ህሊና ከቶውንም ሊጠፋ የማይችል ወንጀል። በቀን እስከ አምስት መቶ ህዝብ የሚገደልበት ወንጀል። በመቶ ሺህ የሚጠጉ ዜጎች በፈረቃ የሚታሰሩበት እና የሚሰቃዩበት ወንጀል። ዘርፈውም፣ ገድለውም፣ አስረውም መዝለቅ እንደሚችሉ የተማመኑ ይመስላል። ግን ለውጥ የተፈጥሮ ህግ ነውና መምጣቱ አይቀሬ ነው። የግዜ ጉዳይ እንጂ ከፍትህ አያመልጡም።

ግዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ነውና፣ ግዜው ደርሶ እስኪወድቁ ድረስ እነሆ በ”ማስረጃ የለም!” ዘፈን ይጨፍራሉ።

Filed Under: TIGRINJA


Do you have questions?  Feel free to contact us!

 [ssba]

WELCOME!

Hummingbirdlogo140906_edited-1Africa Horn Now (AHN) is an independent online publication focused on raising major news and views affecting the lives and times of people living in the African Horn. AHN (https://ahn.nu) goes farther and digs deeper to bring you stories that matter. AHN offers reads that inform, inspire and empower! Sweden is home of https://africahornnow.com.

QUICK MEDIA LINKS (TV/RADIO)

Radio Sweden

EriTv

ድምፂ ረድዮ ኣሜሪካ (VOA Tigrigna)

Radio Erena

ፕሮግራም ሬድዮ መድረኽ (Radio EriMedrek)

ዶይቸ ቬለ (DW Amharic)

EBC TV (Ethiopia)

VOA Afaan Oromoo

VOA/Amharic የአሜሪካ ድምፅ

ESAT Radio

Citizen TV  (Kenya)

NTV (Uganda)

South Sudan TV

Universal Somali TV

SABC (South Africa)

Russia Today

Aljazeera (English)

Aljazeera (الجزيرة نت)

Radio France International (RFI)

France 24

NPR

PBS

BBC

CNN

CCTV (China)

AHN-Weather

 

Archives

  • May 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • July 2020
  • June 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • June 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • April 2018
  • March 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • December 2017
  • November 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • December 2016
  • November 2016
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • July 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • February 2016
  • January 2016
  • December 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • July 2015
  • June 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • March 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • July 2014
  • May 2014
  • March 2014

Tags

aAfrican politics Africa ANC Angola Authoritarian constitutions Authoritarianism not key to China’s economic success authoritarian regimes Authoritarian State authoritarian states Burundi Competitive authoritarian COMPETITIVE AUTHORITARIANISM Covid-19 democratic government and society Earthquake economy Egypt elections Eritrea Ethiopia FEEDING THE DRAGON Greece hybrid regime type India Kenya Mugabe Nepal new sort of authoritarian rule Nigeria North Korea opposition Pierre Nkurumziza Postcolonial Africa Postcolonial African regimes Presidential Election 2015 Quake repressing civil society and silencing dissent Rwanda South Africa Types of Authoritarian regimes Uhuru US US Trip women's league Zimbabwe

Recent Posts

  • ካብ ውሽጢ ቤት ማእሰርታት ኤርትራ

    May 6, 2021
  • Sudan announces failure of GERD negotiations, returns file to African Union

    November 6, 2020
  • Satellite data provides fresh insights into the amount of water in the Nile basin

    November 6, 2020
  • A New Administration Won’t Heal American Democracy

    November 6, 2020
  • Ethiopia blasts Trump remark that Egypt will ‘blow up’ dam

    October 24, 2020
[ssba]

Contact

[contact-form to=’editor@africahornnow.com’ subject=’Contact from africahornnow contact page’][contact-field label=’Name’ type=’name’ required=’1’/][contact-field label=’Email’ type=’email’ required=’1’/][contact-field label=’Comment’ type=’textarea’ required=’1’/][/contact-form]

Log In

Copyright © 2022 Africa Horn Now · WordPress · Log in